Integrated solutions for Agricultural Developemnt በኢትዮጵያ
ኦንላይን
የግብርና ትምህርት
በዚህ የኦንላይን የግብርና ትምህርት በማንኛውም ደረጃ የሚገኙ የግብርና ባለሙያዎች ፤ ለግብርና አስፈላጊ የሆኑ ክህሎቶችን በመውሰድ ክህሎታቸውን ያዳብራሉ።
የ ISAD ኦንላይን የግብርና ትምህርት መድረክ – ይማሩ ፣ ይደጉ ፣ ያሳኩ
ጀማሪ ለሆኑ እንዲሁም ትጨማሪ ክህሎቶችን ማሳደግ ለሚፈልጉ የግብርና ባለሙያዎች ISAD ኦንላይን የትምህርት መድረክ ለሁሉም ደረጃዎች የተዘጋጀ እና በባለሙያዎች የሚመራ የግብርና ትምህርትን ያቀርባል። በተጨማሪም ወጣቶች በዘመናዊ ግብርና ስልት ውስጥ ራሳቸውን እንዲያሳድጉ እንዲሁም ግብርናውን እንድያቀላጥፉ የሚያስችላቸውን እውቀት እና ክህሎት በማቅረብ ለአዲሱ የግብርና ስልት መንገድ ይጠርጋል።
የምንሰጣቸው አገልግሎቶች:
- ከጀማሪ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ያሉ የግብርና ትምህርቶች
- በብቁ ባለሙያዎች እርዳታ የሚሰጡ ተግባር ተኮር ስልጠናዎች
- አሳታፊና የሚበረታቱ የትምህርት ልምዶች
- ለሙያዊ እድገት የሚያግዙ የምስክር ወረቀቶች
- ባለሙያዎች ጋር ትስስር መፍጠር
የአገልግሎታችን ተጠቃሚዎች
የ ISAD ኦንላይን የግብርና ትምሀርት መድረክ በተለያዩ የትምህርት እና የሙያ ደረጃዎች ላይ ላሉ ሰዎች የተዘጋጀ ሲሆን፣ ከነዚህም መካከል:
በግብርና እና የግብርና ንግድ ፍላጎት ያላቸው ወጣቶች
ገበሬዎች
አዲስ እና በስራው ለምድ ያካበቱ ስራ ፈጣሪዎች
የግብርና ተማሪዎች እና ተመራማሪዎች
መንግስት እና የልማት ድርጅቶች
የትኩረት አቅጣጫዎች
ISAD የኦንላይን የግብርና ትምህርት ለግብርና ብቁ የሆኑ ባልሙያዎችን በመፍጠር የግብርና ዘርፍ ልማትን የማሳድግ ዓላምን ሰንቆ በቁርጠኝነት ይንቀሳቀሳል፡፡
ዘላቂ እና ፈጠራ ያለው የግብርና ስራ
አካባቢያዊ ጥበቃን በመተግበር ምርታማነትን የሚጨምሩ ዘመናዊ ዘዴዎችን ማስተዋወቅ፡፡
ለሁሉም ደረጃዎች ተደራሽ የሆነ ትምህርት
ለገበሬዎች ፣ የግብርና ስራ ፈጣሪዎች እና ተመራማሪዎች የተዘጋጀ ከጀማሪ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ጥልቀት ያላቸው ትምህርቶች።
በቴክኖሎጂ የተመራ የግብርና መፍትሄዎች
ዘመናዊ የግብርና መሣሪያዎች፣ ትክክለኛ ግብርና እና ዲጂታል መፍትሄዎችን በማዋሃድ ውጤታማነትን ማሳደግ።
ወጣቶችን ባመሰልጠን ለግብራና ሰራ ማብቃት
ወጣቶች ወደ ግብርና ንግድ የሚያምሩ ሙያዊ ክህሎቶችን መግንባት እና እድሎችን በማመቻችት በቂ ድጋፍ መስጠት።