ስለ ISAD ኢትዮጵያ
ISAD ኦንላይን የትምህርት መድረክ በዘርፉ በቂ ልምድ ባካብቱ የግብርና ባለሙያዎች በማታገዝ የግብርናው ዘርፍ ቀጣይነት ባለውና ፈጠራን በተሞላ መንግድ እንዲቀጥል በማድረግ ማህበረሰብን ለማገልገል ቆርጦ የተነሳ ነው።
- የግብርና ፈጠራዎችን ማራመድ
- ዘላቂ የግብርና ልምዶችን ማስተዋውቅ
- ገበሬዎችን ልንግድ በማብቃት ማደራጀት
- በባለሙያ የታገዘ ስልጠና እና የምክር አገልግሎት
- ቴክኖሎጂን በመጠቀም ዘመናዊ ግብርና ማሳደግ
- የገበያ ግንኙነቶችን ማጎልበት
የእኛ ታሪክ
ISAD በእዩኤል ተገኑ እና በአብርሃም ሙላቱ በግብርና ላይ ትልቅ ፍቅር ባላቸው ስዎች በ2015 ዓ.ም ተመሰረተ። እነዚህ ህልመኞች በግብርናው ዘርፍ ለመጓዝ ተገቢውን መረጃ ለማግኘት ቢሞክሩም በሀገራቸው ይሀን ማግኘት አዳጋች ሆኖባቸው አልፏል። ይህ ፈተና የISAD ሀሳብ እንዲመንጭ ምክንያት ሆነ። ለአዲስ እና አሁን በዘርፉ ላሉ ገበሬዎች፣ የግብርና ስራ ተማሪዎች እና ተመራማሪዎች ቀላል፣ ጥራት ያለው የግብርና ትምህርት የሚሰጥ ኦንላይን መድረክ። ከዛን ጊዜ ጀምሮ፣ በፈጠራ እና በባለሙያዊነት ግብርናን ለመቀየር የሚያስችል የእውቀት ማዕከል ለመገንባት በቆራረጥ እየሠራን ነው።
እዩኤል ተገኑ
አብርሃም ሙላቱ
የእኛ ተልእኮ
በ ISAD፣ እውቀት የግብርና ለውጥ መልክተኛ እንደሆነ እናምናለን። ተልእኳችን ውጤታማ፣ ተግባራዊ እና በምርምር የተረጋገጠ የግብርና እውቀትን በማሰራጨት ምርታማነትን ማሳደግ፣ የምግብ ዋስትናን ማሻሻል እና በመላው ኢትዮጵያ ዘላቂ የግብርና ልምዶችን ማስተዋወቅ ነው። ጥራት ያለው የግብርና ትምህርት ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን እንተጋለን፤ ግብርና ለመጀመር የሚፈልጉ ጀማሪዎች እስከ ንግዳቸውን ለማሳደግ የሚፈልጉ ባለሙያ ገበሬዎች ድረስ ተደራሽ የምሆነ ትለኮ ገንብተናል።
የእኛ ዓላማ
በሚቀጥሉት አምስት አስርት ዓመታት፣ ISAD የግብርና ትምህርት ከቴክኖሎጂ በማዋሃድ የግብርናው ዘርፍ አሁን ካለበት በብዙ እጥፍ እድገት እንዲያሳይ ረዕይ ስንቅን እንሰራለን።
- በቴክኖሎጂ የተሻሻለ የትምህርት ስርዓቶችን በመገንባት የግብርና ትምህርት ተግባራዊ እና የበለጠ ቀላል ማድረግ።
- ማህበረሰባችንን ዘመናዊ የግብርና ቴክኒኮች በማስተማር አብቅቶ ማደራጀት።
- ለመጀመር ወይም ስራቸውን ለማሳደግ የሚፈልጉ ገበሬዎች፣ የግብርና ስራ አስኪያጆች እና ተከታዮች ዋና አጋር ሆኖ መቆየት።
ለምን ISADን የመጀመርያ ምርጫዎ ያደርጋሉ?
ተደራሽነት
በኦንላይን ድረገፅ በማንኛውም ቦታ እንዲሁም ብሚምቻቹ ግዜ ተድራሽ በመሆኑ።
ብቁ አሰልጣኞች
በዘርፉ በከፍተኛ ደርጃ ከሚግኙ የግብርና ባለሙያዎች እውቀትና የምክር አግልግሎት ስለሚያገኙ
ደርጃን መሰረት ያደረገ ትምህርት
ጀማሪ ወይም በግብርናው ዘርፍ በዙ ዓመታትን የቆዩ ቢሆኑም፣ ለእርስዎ የተሟላ የትምህርት ፕሮግራሞች ስላሉን።
የምህበረሰብ ግንባታ
በግብርናው ላይ ፍላጎት ካልቸው እንዲሁም በዝርፉ ብዙ ዓምታት ከሰሩ ሰዎች ጋር የመገናኝት እድል ሰለሚያገኙ።